Konjit Teshome

በርዋንዳ ባለፉት ስድስት ሳምንታት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በመዝነቡ ምክንያት 46 ሰዎች መሞታቸውንና 127 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን ከሀገሪቱ የአደጋዎች ቁጥጥርና ስደተኞች ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣ መረጃ ያመለክታል፡፡ በተመሳሳይ ወቅት 64 መኖሪያ ቤቶች ሲወድሙ፤ ሌሎች 2.955 የሚሆኑት ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በ121 ሄክታር የእርሻ መሬት ላይም ውድመት ደርሷል፡፡