በዩጋንዳ የጠፋውን ሐይቅ ለመመለስ የስደተኞቹ ፍሬያማ ጥረት
A woman collects water for domestic use at one of the fishing grounds along Lake Nakivale

የናኪቫሌ ሐይቅ በደቡባዊ ዩጋንዳ ኮኪ ሐይቆች በመባል የሚታወቀውን ሐይቅን ከፈጠሩ አራት ትናንሽ ሐይቆች መካከል አንደኛው ነው፡፡ በ26ኪሜ ስኩዌር ቦታ ላይ ያለው ሐይቁ፤ 14 ኪ.ሜ ርዝመት፣ 6 ኪሜ ስፋት እና የውሀ መጠኑ ከፍተኛ ሲሆን 3.5 ሜ ጥልቀት ያለው ነው፡፡ በኢሲንጊሮ ወረዳ የሚገኘው የናኪቫሌ ሐይቅ፤ በናኪቫሌ ስደተኞች ካምፕ የሚገኙትን ስደተኞችንና በሐይቁ አቅራቢያ የሚኖሩ የሀገሬውን ዜጎችንም የሚያገለግል ነው፡፡

ሐይቁ መድረቅ የጀመረው የስደተኞች ካምፕ በሚቋቋምበት ጊዜ የተፈጠረው ከፍተኛ የደን መራቆት ያስከተለው ደለል በመበከሉ ነው፡፡ 

በሐይቁ ዳርቻዎች ዙሪያ በስደተኞችም ሆነ በሀገሬው ነዋሪዎች የሚፈጸሙ መሬቱን የማረስ፣ ከመጠን በላይ እና ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ የአሳ ማርባት እንቅስቃሴዎች ደግሞ ሁኔታውን የከፋ አድርገውታል፡፡

አሁን በናኪቫሌ የስደተኞች መጠለያ ያሉ ስደተኞች ለእነሱም ሆነ ለአካባቢው ነዋሪዎች ዋንኛ የውሀ ምንጭ የሆነውን ሐይቅ ለመታደግ የበኩላቸውን ሚና መጫወት ጀምረዋል፡፡

ሐይቁን የመጠበቅና መልሶ የማልማት ስራ

የርዋንዳ ስደተኛ የሆነው ኢኖክ ትዋጊራዬሱ የስደተኞች የአካባቢ ጥበቃ አንቂ ማህበረሰብ አቀፍ ድርጅት የሆነው የናኪቫሌ አረንጓዴ አካባቢ (Nakivale Green Environment) ሰብሳቢ ሲሆን፤ ከሰዎች እንቅስቃሴ ነጻ በሆነው የሐይቁ 200 ራዲየስ በሆነ ቦታ ላይ እስከ አሁን ድረስ ወደ 60,000 የሚጠጉ የዛፍ ችግኞችን እንደተከሉ አስታውቋል፡፡ ዛፎቹ ለማገዶነት እና ለቤት መስሪያነት የላቀ ጠቀሜታ እንደሚሰጣቸውም ተናግሯል፡፡

“ከዚህ በፊት ስኳር ድንች፣ ቲማቲም እና ሌሎች አትክልቶችን እንተክል ነበር፡፡ የጓሮ አትክልታችን መሬታችንም እስከ ሐይቁ ድረስ ይጠጋ ነበር፡፡ የሐይቁን ዙሪያ መንከባከብ ከጀመርን በኋላ ግን የሐይቁ ውሀ መጠን እየጨመረ መጥቷል” ይላል ትዋጊራየሱ፡፡ በዚህ አመትም የቡድናቸው የመጨረሻው ችግኝ ተከላ አመት ሲሆን፤ 40,000 ችግኞችን ለመትከል አቅደዋል፡፡ 

“በዚህ አመት መጨረሻ ላይ በናኪቫሌ ሐይቅ ዙሪያ 100,000 በላይ ዛፎችን እንተክላለን፡፡ ይህም 5ኪሎ ሜትር ራዲየስ ይሸፍናል፡፡ ዛፎችን በመትከል በምናገኘው ገቢ በመጠለያ ጣቢያው የአረንጓዴ አካባቢ ማዕከል ለማቋቋም አስበናል፡፡ ይህ ደግሞ የአናጺነትና የቆራጭነት ሙያ ላላቸው ሰዎች የስራ እድል በመስጠት በሐይቁ ላይ ጥገኛ የሆኑ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ ያስችላል” በማለት ትዋጊራየሱ ይናገራል፡፡ 

የዛፍ ችግኙ ፕሮጀክት በምግብ እና አትክልቶች ተከላ በማድረግም የተደገፈ ነው፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩት ዛፎቹ ከ5-10 አመታት እስኪያድጉ እየጠበቁ ለአጭር ጊዜ የሚሆናቸውን ምግብ እና ገንዘብ ያገኙበታል፡፡

“አረንጓዴ ቃሪያ፣ ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ በቆሎ፣ እና ጥቅል ጎመን በተወሰነ ቦታ ላይ እንተክላለን” የሚለው ትዋጊራየሱ፤ “አትክልቶቹን ውሀ በማጠጣት በምንከባከብበት ጊዜ ዛፎቹም ተጠቃሚ ይሆናሉ” ሲል አብራርቷል፡፡

የናኪቫሌ ስደተኞች መጠለያ በዋነኛነት የተቋቋመው የቱትሲ ሀረግ ላላቸው ርዋንዳውያን በ1963 ነበር፡፡ ነገር ግን በጊዜ ብዛት አሁን ላይ ከርዋንዳ፣ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ከሶማሊያ፣ ከሱዳን፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኬንያ እና ከኤርትራ ጨምሮ ከሰባት በላይ ሀገሮች ለመጡ ስደተኞች መጠለያ ሆኗል፡፡

በዩጋንዳ የሚገኙ ስደተኞችን ቁጥር በተመለከተ የአለም ባንክ መረጃን World Bank data ስንመለከት ከ2010 ጀምሮ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፤ በ2019 ቁጥሩ 1,359,458 መድረሱን ያመለክታል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን በመስከረም ወር በ 2020 report የወጣ ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ፤ በናኪቫሌ የስደተኞች ጣቢያ የሚገኙ ስደተኞች ቁጥር 134,1999 ነው፡፡ ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የህዝብ ብዛት ደግሞ በሐይቁ ላይ ጫና አሳድሯል፡፡

!function(e,i,n,s){var t="InfogramEmbeds",d=e.getElementsByTagName("script")[0];if(window[t]&&window[t].initialized)window[t].process&&window[t].process();else if(!e.getElementById(n)){var o=e.createElement("script");o.async=1,o.id=n,o.src="https://e.infogram.com/js/dist/embed-loader-min.js",d.parentNode.insertBefore(o,d)}}(document,0,"infogram-async");

በናኪቫሌ ሐይቅ ላይ በጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ እና በብሔራዊ የአሳ እርባታ ሐብት ምርምር ማዕከል ይፋ የሆነ የ2010 ሪፖርት ( A 2010 report )  በ80 አመታት ውስጥ በውሀው ጥራት ላይ ለውጥ መከሰቱን ያሳያል፡፡

አኪቴንግ ኮንስታንስ በናኪቫሌ ስደተኞች ጣቢያ የአካባቢ ጥበቃ ረዳት ኦፊሰር ናቸው፡፡ በረግረጋማው የናኪቫሌ ሐይቅ ዙሪያ ጫና ለመፈጠሩ ለህዝብ ብዛት መጨመር እና የመጠለያ ጣቢያው አብዛኛው ለም አፈር መጥፋት አስተዋጽኦ ማድረጉን ያስረዳሉ፡፡

“እስከአሁን ድረስ የሐይቁን 7ኪሎ ሜትር ውሀ ለመመለስ ሞክረናል፡፡ እዚህ አካባቢ ዛፎችን ተክለናል፣ የረግረጋማ ቦታዎች እንክብካቤ እና የሐይቁን ወሰን ልየታ አድርገናል፡፡ እንዲሁም ደግሞ ሐይቁን መልሶ ማልማት የሚኖረውን ፋይዳ በተመለከተ ህዝቡ ግንዛቤ እንዲኖረው አድርገናል” በማለት አኪቴንግ የሰሩት ስራዎች ይገልጻሉ፡፡

ሐይቁን መልሶ የማልማት ጥቅሞች

ጆሹዋ ንዛሆ ኦዊማና የርዋንዳ ስደተኛ እና የናኪቫሌ አረንጓዴ አካባቢ አባል ነው፡፡ መንግስት መሬት በመስጠት እገዛ ማድረጉን እና በካምፑ ድጋፍ ሰጪ የሆነው የንሳሚዚ ማህበራዊ ልማት ማዕከል፤ የዛፍ ችግኞች እና የአትክልት ዘሮችን እንደሰጣቸው ይገልጻል፡፡

“በሐይቁ ዳርቻ በምንተክላቸው ተክሎች አማካኝነት ሐይቁ መድረቅ ሲጀምር የብሔራዊ አካባቢ ጥበቃ አስተዳደር ባለስልጣን ከአካባቢው እንድንርቅ ነው ያደረገን፡፡ የዩጋንዳ መንግስት ደግሞ ከሐይቁ 200ሜ ርቀት ላይ ያለ መሬትን እንድንጠቀምበት ፈቀደልን” በማለት የተደረገላቸውን ድጋፍ ያስረዳል፡፡

ንዛሆ አክሎም ከንሳሚዚ በሚያገኙት ድጋፍ ከሐይቁ ዳርቻዎች ራቅ ባለ ቦታ ለሙከራ የአትክልት ልማት ፕሮጀክት መጀመራቸውን ይገልጻል፡፡ ምክንያቱም ከሐይቁ በራቀ ቦታ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ እርግጠኛ አልነበሩምና ነው፡፡

“ወደ አዲሱ የአትክልት ቦታችን ውሀ ወስዶ ማጠጣት በጣም አድካሚ ስለሆነብን ውሀ መሳቢያ መከራየት ነበረብን” በማለት ንዛሆ ጅምራቸውን ያስታውሳል፡፡

አሁን ላይ ግን ድካማቸው ፍሬ አፍርቶ በማየቱ ደስተኛ ሆኗል፡፡

“በሐይቁ ዳርቻዎች ላይ አትክልት ማልማት በመከልከሉ ፈጽሞ አንጸጸትም፡፡ ዛፎቻችን እና አትክልቶቻችን በጥሩ ሁኔታ እያደጉ ነው፡፡ የናኪቫሌ ሐይቅ የውሀ መጠንም እንዲሁ እየጨመረ ነው” ይላል ንዛሆ፡፡

ጃኮኒየስ ሙሲንግዊሬ የብሔራዊ አካባቢ ጥበቃ አስተዳደር ባለስልጣን የቀጠናው ማናጀር ናቸው፡፡ “በመጀመሪያው ምዕራፍ ከሰው እንቅስቃሴ ነጻ እንዲሆን በተከለለው ቦታ ላይ ዛፍ ተከላን ማስተዋወቅ ነበረብን፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በዛፎቹ ስር ወቅታዊ ሰብሎችን እንዲያለሙ ፈቅደንላቸው ስለነበር ቦታው በአትክልት የተሞላ ሊሆን ችሏል” ሲሉ ይናገራሉ፡፡

የገጠሙ ፈተናዎች

ካጁምባ ጎድፍሬ

የአካባቢ ጥበቃ ረዳት ኦፊሰሯ አኪቴንግ ኮንስታንስ እንዳስታወቁት የአካባቢው ፖለቲከኞች ውቡን ሐይቅ መልሶ ለማልማት የሚደረገው ጥረትን በተመለከተ ስጋት ነበራቸው፡፡

“የሀገሪቱ ዜጎች በሚኖሩበት ቦታ በጣም ብዙ ክልከላዎች አሉ፡፡ መልሶ የማልማት እንቅስቃሴ ስንጀምር ደግሞ የፖለቲከኞች ጫና ይገጥመናል” በማለት የገጠማቸውን ፈተና ይገልጻሉ፡፡

ምንም እንኳ የናኪቫሌ ሐይቅን ለመታደግ ስደተኞቹ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመደገፍ የሚደረጉ እገዛዎች ቢኖሩም በቂ እንዳልሆነ የአካባቢ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

የኢሲንጊሮ ወረዳ አመራሮች የሐይቁን መልሶ የማልማት ስራን በተለይም ደግሞ በዩጋንዳ ዜጎች በተያዙ አካባቢዎች እንዲያስፋፉ አጥብቀው ይፈልጋሉ፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የቀጠና ማጀር ጃኮኒየስ ሙሲንግዊሬ በበኩላቸው ያለባቸው የገንዘብ እጥረት የናኪቫሌ ሐይቅን ለመጠበቅ አቅም እንዳሳጣቸው ይገልጻሉ፡፡

“ትልቁ ችግራችን የምናገኘው የገንዘብ ድጋፍ በጣም ውስን መሆኑ ነው፡፡ የሐይቁን አካባቢ ለማልማት የምናደርገው እንቅስቃሴ በለጋሾች ድጋፍ ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ የሚደረገው ድጋፍ ሲያበቃ በዘላቂነት ሐይቁን የማልማት ስራው ፈተና ውስጥ ይወድቃል”

በኢሲንጊሮ ወረዳ የፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ተወካይ ኸርበርት ሙሃንጊ በሰጡት አስተያየት፤ “ብሔራዊ የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲው በሐይቁ ዙሪያ 200ሜትር ከልሏል፡፡ ሁሉም ነዋሪ ስተኞችም ሆኑ ዜጎች ይህንንማክበር አለባቸው” ብለዋል፡፡

“ሰዎች ከሚያሳስቷቸው ፖለቲከኞች መራቅ አለባቸው፡፡ ከፕሬዝዳንቱ ቢሮ ድጋፍ ስላለን በኃይልም ቢሆን እናርቃቸዋለን” ብለዋል፡፡ 

ሙሀንጊ አክለውም፤ “የኢሲንጊሮ ነዋሪዎች የናኪቫሌ ሀይቁን መልሶ ለማልማት የሚያፈልገውን ስራ ሁሉ መስራት አለባቸው” ሲሉ አሳስበዋል፡፡ “የናኪቫሌ ሐይቅ ዋንኛው የውሀ ምንጫችን በመሆኑ ደርቆ ከቀረ እኛም ማለቃችን ነው፡፡ ስደተኞቹ ሐይቁን ለመጠበቅ መልካም ተግባሮችን እያደረጉ ነው፡፡ የእኛው ዜጎች ይህንን በጎ መንገድ መከተል አለባቸው”