የሴቤይ ወጣቶች የሰው ልጆች ውጋጅን ወደ ምግብ ማብሰያ ጋዝነት ለውጠዋል

የሴቤይ ወጣቶች የሰው ልጆች ውጋጅን ወደ ምግብ ማብሰያ ጋዝነት ለውጠዋል

በሜላኒ አዩ

በምስራቅ ኡጋንዳ በካፕቾራ ወረዳ በሴቤይ ክፍለ ግዛት ሴቶችን በብዛት ያካተተ የወጣቶች ቡድን ከጸሐይ ብርሀን የሚገኝ ሀይልን በመጠቀም የሰው ልጅና እንስሳት ውጋጅን ማለትም ሽንትና ሰገራን ወደ ብቁ የምግብ ማብሰያ ጋዝነት የሚቀይር አዲስ ፕሮጀክትን ጀምረዋል፡፡

በቅርቡ ሀገር በቀል የህብረተሰብ ኢንተርፕራይዝ የሚሆነውና ለማህበረሰብ ጠቀሜታ የሚሰጠውና ትርፍ የሚያስገኘው ኩባንያ ፒክ ኢት ክሊን ከሁለት አመት በፊት ሲቋቋም ጥሩ የንጽህና አጠባበቅ ለጎደላቸው መኖሪያ ቤቶች ተንቀሳቃሽ መጸዳጃ ቤቶችን በማቅረብ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የከብት እንስሳት ላላቸው ነዋሪዎች የእንስሳቱን እዳሪ ወይም እበቱን የሚያስቀምጡበት መያዣዎችን አቅርቧል፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ዘጋቢያችን ሜላኒ አዩ በዚህ የፈጠራ ሃሳብ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ዘገባን አጠናክራለች፡፡

ከካምፓላ ከተማ በሰሜን ምስራቅ 225 ኪሜ አካባቢ ርቃ በምትገኘው ካፕቾርዋ ከተማ ፒክ ኢት ክሊን ኢንተርፕራይዝ ለአካባቢው ማህረሰብ በተለይም በገበሬዎች ዘንድ እንደ ትልቅ ሀብት ነው የሚታየው፡፡ 

በዝናባማ ወቅት ከፍተኛ ሙቀት ተከሰተ ማለት በሴቤይ ክልል ለገበሬዎች የመዝሪያ ጊዜያቸውን የሚያራዝም ሲሆን፤ አሁንም ድረስ አዲሱ ወቅት ከመጠን በላይ የሆነውን ዝናብ እያሳየን ነው፡፡

ዊሊያም ቼሌንጋት በ30 አመት የግብርና ህይወታቸው እንዳለፉት ሶስት አመታት በቆሎ ለመዝራት ዘግይተው እንደማያውቁ ይናገራሉ፡፡

‹‹የገበሬው ማህበረሰብ ከ15 አመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በቂ ነገር የለውም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሲዘንብ አንዳንዴ ከመጠን በላይ ይዘንባል፡፡ ይኽም ሰብሎች ከመጠን በላይ እንዲያድጉ ወይም እንዳይበቅሉ ያደርጋቸዋል›› በማለት የ75 አመቱ አዛውንት ችግሩን ያስረዳሉ፡፡

‹‹ጸሐያማ ሲሆን ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ለረጅም ጊዜ በመቆየት ሰብሎቹን ያጠወልጋቸዋል›› በማለት ተስፋ የቆረጡት የካሴሬም ኤሪያ ኮኦፐሬቲቭ (ካሴ) ስራ አስኪያጅ ዩሱፍ መሐመድ ሙዶንዶ ከሪፖርተራችን ጋር በአደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡

ሙዶንዶ እንዳስታወቁት በካሴ ብቻ ገበሬዎች በመጀመሪያው ወቅት 500 ሔክታር ቶን በቆሎ መሰብሰብ የቻሉ ሲሆን፤ ይህም ከሚጠበቀው 700 ሜትሪክ ቶን በታች ነው፡፡ ባቄላ የሚያመርቱት ደግሞ ባለፈው አመት ለወትሮው ከሚያገኙት 200 ሜትሪክ ቶን ማረምት የቻሉት 140 ሜትሪክ ቶን ነው፡፡

Copy of Story 3 viz 1

በዚህ እውነታ መነሻነት ታይቶ የማይታወቅ የአየር ንብረት ሁኔታ ገበሬዎችን ተስፋ አስቆርጧል፡፡ ምርታቸውን በመቀነስም ለረሀብ በር ከፍቷል፡፡

የአካባቢው ወጣት ወንድና ሴቶች ማህበረሰባቸው ለተጋረጠበት ከፍተኛ የአየር ንብረት ለውጥ ጥያቄዎች ለተወሰኑት ምላሽ ለመስጠት የሚችል እንደሆነ በማመን ነው አዲስ የፈጠራ ግኝት ይዘው የተገኙት፡፡

የቡድኑ አባላት እንደሚናገሩት የአየር ንብረት መጠንን ሊጨምር ይችላል ያሉትን የማህበረሰቡን ዛፍን የመቁረጥ ልማድ እንዲቀንስ አሊያም ጨርሶ እንዲወገድ ለማስቻል የሚያደርጉት ጥረት ነው፡፡ 

የቡድኑ መሪ ጆአን ቼመስቶ ፒክ ኢት ክሊን ተብሎ የሚጠራው የሴቤይ ወጣቶች የባዮ ጋዝ ፕሮጀክት ለከሰልና ለማገዶነት ተብሎ የሚቆረጠውን ዛፍ ለመታደግ እንደሚችል ያምናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በማህበረሰባቸው ዘንድ መጸዳጃ ቤት የሌላቸውን መጸዳጃ ቦታቸውን ማሻሻል ለውጥ የሚፈጥር እርምጃ መሆኑን ተረድተዋል፡፡

የቡድኑ አባላት ይህንን አገልግሎት የሚጠቀሙ ከ350 በላይ ደምበኞችን ማግኘት ችለዋል፡፡

ይህ ፕሮጀክት በምስራቅ ኡጋንዳ በሴቤይ ክፍለ ግዛት በአይነቱ የመጀመሪያ ሲሆን፤ ከሁለት አመት በፊት እንደመጀመሩ አገልግሎቱን ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት ታይቷል፡፡ በመሆኑም የዚህ አካባቢ ማህበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥ ትርጉምን ማድነቅና መረዳት ለመጀመሩ አይነተኛ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡

‹‹የወደፊቱ እጣ ፈንታችን የሚቀረጸው መሬት ላይ በምናየው እውነታ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የአካባቢያችን ማህበረሰብ ፈጠራችንን ማድነቅና መጠቀም ጀምሯል›› የሚለው የሴቤይ የወጣቶች ባዮ ጋዝ ፓወር ፕሮጀክት ሀላፊ ዊሊያም ቼፕቴኦክ ነው፡፡

ቼፕቴኦክ እንደገለጸው ሁልጊዜም ቢሆን ከአላስፈላጊ የህዝብ ጥርጣሬና ጫና ለመዳን ራሳቸውን ዝቅ አድርው እየሰሩ መቀጠል የሁልጊዜም እቅዳቸው ነበር፡፡

‹‹ሁልጊዜም ማንኛውም የውጭ አካል የቡድን መንፈሳችንን ሳይረብሸው እኛው ራሳችን ስህተቶቻችንን መስራትና ለማስተካከል እና ልንማርባቸወ ነው የምንፈልገው፡፡ በእርግጥ በመጨረሻም ራሳችንን እዚህ ደረጃ በማግኘታችን እንኮራለን፡፡ ግን ደግሞ ብዙ የምንፈልገውና የምንሰራው ብዙ ነገር አለ›› ሲል ቼፕቴቾግ ጨምሮ ተናግሯል፡፡ 

ቡድኑ 10 አባላትን ያካተተ ሲሆን ሰባት ሴቶችና ሶስት ወንች ናቸው፡፡ አብዛኞቹም ስራ አጥ የዩኒቨርስቲ ምሩቃን ነበሩ፡፡ ሰባቱ አባላት ዩኒቨርስቲ ያጠኑት ግብርና ወይም ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ነው፡፡

እንደ ቼመስቶ ገለጻ የአየር ንብረት ተጽዕኖ በማህበረሰባቸው ላይ ባስከተለው አስደንጋጭ አደጋን ለማቋረጥ የተገደዱት፡፡ የባዮ ጋዝ ሀይል ማመንጫ ከመስራታቸው በፊት በአየር ንብረት ዙሪያ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በመስራት ነው የጀመሩት፡፡

በአካባቢው የተሰሩት መጸዳጃ ቤቶች ‹‹ብሉ ቦክስስ›› (ሰማያዊ ሳጥኖች) በመባል የሚጠሩ ሲሆን ተንቀሳቃሽ እና ቱቦን የማይፈልጉ ናቸው፡፡

ቀጥሎም የተጠራቀመው ውጋጅ ወደ ማሽኖች ውስጥ ከመግባታቸው በፊት በቡድኑ አባላት አማካኝነት ከሰማያዊ ሳጥኖቹ ይሰበሰባሉ፡፡ ሽንት ቤቱን ለመጠቀም አንድ ደንበኛ በወር ወይም በመረጠው በአመታዊ ክፍያ 10.800 የዩጋንዳ ሽልንግ (3 የአሜሪካና ዶላር) በወር ይከፍላል፡፡ 

ይኸውም አንድ ተጠቃሚ አጠቃላይ ለአመት የሚከፍለው ገንዘብ መጠን 129.600 የዩጋንዳ ሽልንግ (36 የአሜሪካ ዶላር) ነው፡፡

ተጠቃሚዎች ትዕዛዛቸውን ማቋረጥ የሚችሉ ሲሆን፤ መልሰው አገልግሎቱን ማግኘት ከፈለጉ ከቀድሞው ከፍ ያለ መጠን እንዲከፍሉ የሚደረግ መሆኑ በኢኒሺዬቲቩ በተዘጋጀው በደንብና ህጎች ላይ ተቀምጧል፡፡

በኬንያ ከአምስት አመት በታ ያሉ ህጻናት ሞት መንስኤ ከሆኑት ምክንያቶች ዋንኛው በደካማ ንጽህና ጉድለት አማካኝት በሚከሰተው ተቅማጥ እንደሆነ የምባሌ ሪፈራል ሆስፒታል ዶክተር ቢያትሪስ አጉቲ ገልጸዋል፡፡ ከፊል ከተማ የሆኑት አብዛኞቹ ቤቶች የተከለለ መጸዳጃ ቤት የላቸውም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ምንም ምርጫ የላቸውም ግን ሜዳ ላይ ይጸዳዳሉ ብለዋል፡፡

‹‹አስተማማኝ አወጋገድ ተቅማጥን ለመከላከል የሚያስችል አንደኛው የተሻለ መንገድ ነው፡፡ ይህ ደግሞ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ለአብዛኞቹ በከፊል ከተማ ነዋሪዎች ፈታኝ ነው›› ሲሉ አጉቲ ተናግረዋል፡፡ 

ቼመስቶ እንዳስታወቁት ሀብቶችን ለማስተባበርና የአካባቢው ማህረሰብ አባላት የፕሮጀክቱ አካል እንዲሆኑ ለማሳመን ስድስት ወራትን ይፈጃል፡፡

Patrick Chemonges one of the team members feeds empty plastic water bottles into the chrushing machine

እንደዚህ ያለ ፕሮጀክት ይዞ ለመስራት የገንዘብ መጠኑ ምን ያህል እንደሆነ ተጠይቀውም ቼመስቶ በሰጡት ምላሽ ከ15 ሚሊዮን የዩጋንዳ ሽልንግ በላይ (4.166.6 የአሜሪካን ዶላር) መሆኑን ነው የገለጹት፡፡ ይህ ገንዘብ ጥቂት ማሽኖችን ለመግዛት፣ ለቦታ ኪራይ ክፍያ፣ ለቁሻሻ ማጠራቀሚያዎች ግዢና ለጉልበት ሰራተኞች ክፍያ እንደረዳቸው አስረድተዋል፡፡ 

ወደ 6 የሚጠጉ መጸዳጃ ቤቶች እስከአሁን የቀረቡ ሲሆን፤ ከ300 በላይ ሰዎችን ማገልገል ችለዋል፡፡ ነገር ግን የንጽህና አጠባበቅን ለማሻሻል ከመጸዳጃ ቤቶቹ ቁሻሻው ከተሰበሰበ በኋላ የሚፈጠረው ነገር ነው ንጽህና አጠባበቅን ለማሻሻል ፕሮጀክቱ ቀላል ጥረትም በላይ እንደሆነ የሚያደርገው፡፡ 

ማዋሀድ፣ ማብሰልና ማቃጠል

ውጋጁ ከከሰል ዱቄት እና ከአቅራቢያቸው ከሚገኘው የአበባ እርሻ ተቃጥለው እና ወደ ጥሩ አመድነት የተቀየሩ ተክሎች ጋር ይዋሀዳል፡፡

ፒክ ኢት ክሊን የጸሐይን ጨረሮች በመሰብሰብ የሽንት ቤቱን ውጋጅ በማሞቅ ወደ ከፍተኛ ሙቀት በመጨመር፣ ቀቅሎ በማጽዳት ለድጋሚ አገልግሎት ዝግጁ ይሆናል፡፡

ውህዱም ወደ ጭስ አልባ የጡብ ከሰልነት የሚቀየር ሲሆን፤ ሰዎችም ለቤታቸው ምግብ ማብሰያነት ይገዙታል፡፡ 

የሰዎችን ውጋጅ በመጠቀም ወደ ጠጣር ጋዝነት በመቀየር የእነሱ ፕሮጀክት አንኛው እንደሆነ ቼመስቶ ይናገራል፡፡

በካፕቾርዋ ግዛት የአምስት ልጆች እናት የሆነችው ኖራህ ቼሌጋንት ሰማያዊ ሳጥን መጸዳጃ ቤትን በመኖሪያ ቤቷ በመጠቀም በፒክ ኢት ክሊን የጡብ ከሰል በማብሰል ለአንድ አመት ስትጠቀም ቆይታለች፡፡

‹‹መጸዳጃ ቤቱ ተንቀሳቃሽ ሆነ ማለት በየትኛውም የመኖሪያ ቤታችን ክፍል ልንጠቀምበት እንችላለን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ መጸዳጃ ቤቱን ውጪ ስለመጠቀም የሚያሳስብ አይሆንም›› ስትል ተናግራለች፡፡ 

ቼሌንጋት ስጋ ለማብሰል ግማሽ ኪሉ የጡብ ከሰል ትጠቀማለች፡፡ ምንም እንኳ ዋጋው 900 ሽልንግ (0.25 ዶላር) ለመደበኛው ከሰል ከምትከፍለው ትንሽ ከፍ ቢልም እሳቱ ግን እስከ አራት ሰአታት ያህል የሚቆይ ነው፡፡

‹‹ምግብ በምናበስልበት ጊዜ እሳቱ ለረጅም ሰአት የሚቆይ በመሆኑ ጋዝ መጨመር አያስፈልገንም›› በማለት ቼሌንጋት ጥቅሙን ትናገራለች፡፡ ሌላው ጥቅም ደግሞ የጡብ ከሰሎቹ ምንም አይነት ጭስ እና ሽታ የሌላቸው መሆናቸው እንደሆነም አስታውቃለች፡፡ 

ደንበኞች ከከሰል ዋጋ በሚበልጥ ዋጋ የእኛን የጡብ ከሰል ገዝተው ሲጠቀሙ ለረጅም ጊዜ የሚነድ በመሆኑ በወር ውስጥ ለጋዝ ከሚያወጡት ወጪ ከ10 እስከ 15 በመቶ ያህሉን ማትረፍ ይችላሉ›› ሲሉ ቼመስቶ ይናገራሉ፡፡

ሰዎች አገልግሎቱን የሚመርጡት ንጹህ መጸዳጃ ቤት እንዲኖራቸው ስለሚያደርግ እንደሆነ ያምናሉ፡፡                                                                            

ውስንነት

ምንም እንኳ አገልግሎቱ በሀገሪቱ ባሉ አካባቢች በሙሉ በከፍተኛ ስፋትና መጠን ተፈላጊ ቢሆንም የፈጠራ ምርታቸውን ለማስፋት አቅሙ እንደሌላቸው ነው የቡድኑ አባላት የሚናገሩት፡፡

ስራቸውን ለማሳደግ በሀገሪቱ ኤሌትሪክሲቲ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ለመመዝገብ የገንዘብ ውስንነት አለባቸው፡፡ 

የፕሮግራሙ ሀላፊ ኢሳቅ ኪፕሮቲች ወደ ላቀ ታዳሽ ሀይል ምርትና አስተዳደር ለመሻገር ተጨማሪ ስልጠና እንደሚያስፈልጋቸው በመግለጽ ይህ ብቻ ያሰቡትን እንዳያሳኩ የጎተታቸው መሆኑን አስታውቋል፡፡

‹‹ይህንን ፕሮጀክት በ2017 ከጀመርን አንስቶ የገጠመን ፈተና ያለንን ተሰጥኦ ለማሳደግ የምንችልበትን ወጪ መሸፈን አለመቻላችን ነው፡፡ ታዳሽ ሀይሎችን ማንቀሳቀስ የሚያስችለንን እውቀት ለማግኘት ብንችል ደስ ይለናል፡፡ ነገር ግን ለዚያ የሚያስፈልገው ገንዘብ የለንም›› ብሏል፡፡

ምንም እንኳ እዚህ መሰል ፈተናዎች ቢገጥሟቸውም የቡድኑ አባላት አካባቢን ለመጠበቅ ለባዶ የፕላቲክ ጠርሙሶችን ማጨራመት የሚችል ማሽን መከራየት ችለዋል፡፡

‹‹ባዶ የፕላስቲክ ጠርሙሶች ካልተጨራመቱ በጣም አስፈላጊ ቦታዎችን ሊይዙብን ይችላሉ፡፡ መልሰው ጥቅም ላይ ካልዋሉ ደግሞ አካባቢው ላይ ከፍተኛ ጉዳትን የማስከተል አቅም አላቸው›› ሲል ኪፕሮቲች ይገልጻል፡፡

ይህንን መነሻ በማድረግ ‹‹የፕላቲክ ጠርሙሶቹን በማጨራመት በመልሶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በሚያደርጉ መያዣ ቦርሳዎች በማስቀመጥ ቦታን መቆጠብ ይቻላል፡፡ ሀገሪቱም በጣም ብዙ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን መልሳ ጥቅም ላይ ማዋል ትችላለች›› ይላል፡፡

በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች በሲፒ ክፍለ ግዛት የሚገኙት ቡክዎ፣ ክዌን እና ካፕቾርዋ ባሉ ከተሞች ባዶ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን እንዲሰበስቡላቸው ሰዎችን ቀጥረዋል፡፡ ከምባሌ ከተማም የተወሰኑ ባዶ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን ማግኘት ችለዋል፡፡ 

የራሳቸውን የተሞላ ሀይል በመጠቀም ባዶ የፕስቲክ ጠርሙሶቹ እንዲጨራመቱ ይደረጋሉ፡፡

የተጨራመቱት የፕላስቲክ ጠርሙሶች በኪሎ ግራም የሚመዘኑ ሲሆን፤ በየሳምንቱ ከካምፓላ እየመጡ ለሚወስዱ የፕላስቲክ ጠርሙስ ውሀ አምራች ኩባንያዎች ይሸጣሉ፡፡

‹‹ባዶ የፕላስቲክ ጠርሙሶቹን ማጨራመት ያስፈለገበት ምክንያት በጣም ሰፊ ቦታን የሚይዙ ስለሆነ ነው፡፡ ያልተጨፈለቁትን ባዶ የፕላስቲክ ጠርሙሶች ከሲፒ አካባቢ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚፈልገው ድርጅት ያለበት የትኛውም አካባቢ ለማጓጓዝ ጊዜን የሚፈጅ በመሆኑም ነው›› በማለት ኪፕሮቲች አስረድተዋል፡፡

ይሕ ሁሉ ከተሰራ በኋላ ታዲያ ያላቸውን ጠቃሚ የስራ ሀሳቦች በሙሉ ያለ መንግስት፣ የልማት አጋሮችና ህዝብ ድጋፍ አውጥተው መስራት እንደማይችሉ የቡድኑ አባላት ይናገራሉ፡፡

በኢነርጂ ሚንስቴር የካቢኔ አባል ኢሪን ሙሎኒ ለሴቤይ ወጣቶች የባዮ ጋዝ ፕላንት ፕሮጀክት ያደረባቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡

ይሁንና ሙሌኒ የቡድኑ አባላት ጥያቄያቸውን በተቀናጀ ሁኔታ ለመንግስት እንዲያቀርቡ የጠየቁ ሲሆን፤ እንቅስቃሴያቸውን የሚመለከት ቴክኒካል ቡድን ሊመደብና የሚያሳዩትን መሻሻል ለሚኒስትሮችና ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚያሳውቅ ነው የተናገሩት፡፡

‹‹መንግስት እንዲህ ያለውን ሀገር በቀል የፈጠራ ስራ ለማበረታታት ፍጹም ቁርጠኛ ነው፡፡ እኔም ቃል የምገባለችሁ ነገር ቢሯችን በካፕቾርዋ ያለውን ይህንን ፕሮጀክት እንደሚከታተልና ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው› ሲሉ የኢነርጂ ሚንስትሯ ሙሎኒ ተናግረዋል፡፡

Copy of Story 3 viz 3

እንደ ሙሎኒ ሁሉ ድጋፋቸውን የሰጡት የውሀና አካባቢ ሚንስትሩ ሳም ቼፕቶሪስ በማህበረሰቡና ወጣቶቹ የአየር ንብረት ለውጥ እንቅስቃሴ ተደንቀዋል፡፡ ከሴቤይ ክልል የተገኙት ቼፕቶሪስ በሰጡት አስተያየት ቢሯቸው ቡድኑ የሚፈልገውን ማንኛውንም አይነት አስፈላጊ ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው፡፡

እንደ ብሔራዊ የደን ሚንስቴር መረጃ ከሆነ በምስራቅ ዩጋንዳ የሴቤይ ክልል ከቴስቶ ቀጥሉ በደን መራቆት የሚጠቀስ ነው፡፡

ባለስልጣኑ በ2017 በያዘው መረጃ መሰረትም 38 በመቶ የሚሆነው የክልሉ ዛፍና አረንጓዴ ሽፋን ቀንሷል፡፡ 

የሴቤይ የወጣቶች ባዮ ጋዝ ፕሮጀክት የቡድን አባላት ይህ እውነታ በእነሱ ስራ ታሪክ እንደሚሆን በጽኑ ያምናሉ፡፡ ነገር ግን ይህንን ለማሳካት የቴክኒክ፣ ገንዘብና ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡

ይህ ዘገባ የተዘጋጀው በታይም ኤፍኤም ፕሮዳክሽን እና ኤልጎን ዴይሊ ለትርፍ ካልተቋቋመው ድርጅት ኢንፎናይል ድጋፍ ነው፡፡

Like this article?

Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp

Leave a comment

Related Posts