የህዳሴው ግድብ ግብጽን እንደማይጎዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ

ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝን በመገደብ የምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግብጽ በምታገኘው የውሀ አቅርቦት ድርሻ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንደማያደርስ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ሱዳንን ወይም ግብጽን የመጉዳት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላትም ሐሙስ እለት በካርቱም ከሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ጋር ውይይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ገልጸዋል፡፡