በኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን መካከል የተደረገው ስብሰባ በስኬት ተጠናቋል

በቆንጂት ተሾመ

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ አዲስ አበባ ላይ በኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን መካከል የተካሔደው ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ አስታወቁ፡፡ ለ12 ሰአታት የተካሔደው ስብሰባ ሲጠናቀቅ የሶስቱ ሀገሮች ተወካዮች እንደገለጹት ሀገሮቹ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በቀጣይ አብረው ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡